- This event has passed.
Seward Co-op Store Signage Focus Group (Virtual)- Amharic
May 13, 2021 @ 6:00 pm - 7:00 pm
ሰላም ፣ የማህበረሰብ አባላት!
ሲወርድ ኮ-ኦፕ በደቡብ ሚኒያፖልስ ውስጥ በሁለት ቦታዎች ላይ ያለ ንብረትነቱ የማህበረሰብ የሆነ፣ ባለ ሙሉ አገልግሎት የሰቀጣ ሸቀጥ መደብር ነው። ተልዕኳችን ጤናማ ማህበረሰብን ማስቀጠል ነው። ሸማቾች በእኛ መደብሮች ውስጥ የሚፈልጉትን ምርቶች እና አገልግሎቶች እንዲያገኙ ለማገዝ ዲዛይን የተደረገ አዲስ የመደብር ምልክቶችን እየሠራን ነበር። የፕሮጀክቱ ዓላማ በእንግሊዝኛ ላይ ብዙም ጥገኛ ያልሆነ እና የሚነገር ቋንቋ ምንም ይሁን ምን፣ የሰውን ስሜት የሚገልጹ ምልክቶችን መተግበር ነው። የሂደት አካል በማድረግ፣ በሥራችን ላይ ግብረመልስ ለመሰብሰብ ተከታታይ የትኩረት ቡድኖች ውይይቶችን ከህብረተሰቡ አባላት ጋር ማዘጋጀት እንፈልጋለን። ኮ-ኦፕ በአንድ ስብሰባ ውስን ተሳታፊዎችን በመያዝ ስድስት ስብሰባዎችን አዘጋጅቷል። ከእነዚህ ስብሰባዎች መካከል ቢያንስ አንዱ በአማርኛ ፣ በህሞንግ ፣ በኦሮሚኛ ፣ በስፓኒኛ ፣ በሶማልኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የሚመቻች ይሆናል።
ለመሳተፍ ፍላጎት ሊኖራቸው የሚችሉ አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማገናኘት ሊረዱን ይችሉ እንደሆነ እያሰብኩ ነው። የምናገለግላቸውን ጎሮበቶች ብዝሃነትን የሚያንፀባርቁ ግለሰቦችን እንፈልጋለን። ማንንም እንቀበላለን – በተለይም አማርኛ ፣ ህሞንግ ፣ ኦሮሚኛ ፣ ሶማሊኛ እና/ወይም ስፓኒኛ የሚናገሩትን። እያንዳንዱ የትኩረት ቡድን ውይይት 1 ሰዓት ያህል ይወስዳል።
ለእያንዳንዱ የሚሳተፍ ግለሰብ ***የ $50 ሲወርድ ኮ-ኦፕ ስጦታ ካርድ*** እንሰጣለን።
ይህንን ለሌላ ለማስተላለፍ ወይም አንድን ሰው ለእኛ ለመጠቆም ፈቃደኛ ይሆናሉ? እርስዎም እራስዎ ለመሳተፍ ይችላሉ። ከዚህ በታች ያለው፣ ያለሉን ቀናት ናቸው። በ Eventbrite ላይ ለመመዝገብ ስብሰባ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
ስብሰባ 1 (በእንግሊዝኛ የተመቻቸ): 4/27፣ 6 – 7 p.m.
ስብሰባ 2 (በስፓኒኛ የተመቻቸ)፡ 4/28፣ ከ 6 – 7 p.m።
ስብሰባ 3 (በህሞንግ የተመቻቸ)፡ 4/29፣ ከ 6 – 7 p.m።
ስብሰባ 4 (በአማርኛ የተመቻቸ)፡ 5/13፣ ከ 6 – 7 p.m።
ስብሰባ 5 (በሶማልኛ የተመቻቸ)፡ 5/17፣ ከ 6 – 7 p.m።
ስብሰባ 6 (በኦሮምኛ የተመቻቸ)፡ 5/18፣ ከ 6 – 7 p.m።
እርስዎ ወይም አንድ የሚያውቁት ሰው ፍላጎት ካለው እና መሳተፍ ከቻሉ እባክዎን:
ሀ) በጣም በሚመችዎት ቋንቋ ለስብሰባው ይመዝገቡ እና/ወይም
ለ.) ፍላጎት ላለው ሰው ይህንን ያስተላልፉ!
ከግምት ውስጥ ስላስገቡ በጣም እናመሰግናለን!